”ከሰላም ስራቸን ጎን ለጎን የህዝብ የመልማት የመብት ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ አበክረን እንሰራለን”።

”ከሰላም ስራቸን ጎን ለጎን የህዝብ የመልማት የመብት ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ አበክረን እንሰራለን”።

አቶ ሙሀመድ ጀማል

የሚ/ወ/ወ/ውሃና ኢነርጂ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ

በሰሜን ሸዋ ዞን ሚዳ ወረሞ ወረዳ ወረሞ ዋጂቱ ንዑስ ወረዳ ከጃራ እስከ ሬማ ከተማ የሚዘረጋ የንፁህ መጠጥ ውሃ የመስመር ማሻሻያ የፓይፕ ቀበራ ስራ በህብረተሰብ ተሳትፎ ነሀሴ 18/2017 ዓ/ም ማስራት ተችሏል።

የወረዳው ውሃና ኢነርጂ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙሀመድ ጀማል እንደገለፁት ከሰላም ስራችን ጎን ለጎን የህዝብ የመልማት የመብት ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኙ አበክረን እንሰራለን ብለዋል።

የንፁህ መጠጥ ውሃ ማሻሻያ ዝርጋታው 4(አራት) ታንከሮች አሉት ያሉት ኃላፊው ከመነሻው እስከ ሁለተኛው ቡስተን (ታንከር) ድረስ OD 180 PN 25 እና ከሁለተኛው ቡስተን (ታንከር) እስከ ሦሥተኛው ቡስተን (ታንከር) OD 160 PN 25 የሆነ HDP (ፕላስቲክ ፖይፕ) የተዘረጋ ሲሆን ይህንን ፖይፕ ከመሠል አደጋዎች ለመጠበቅ በህብረተሰብ ተሳትፎ የመቅበር ስራ ተከናውኗል።

ይህ የንፁህ መጠጥ ውሃ የማሻሻያ ዝርጋታ ተጠናቆ አገልግሎት መሥጠት ሲጀምር 3(ሦሥት) ቀበሌ ተደራሽ ያደርጋል ሲሉ የገለፁት የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ሙሀመድ ተግባሩን በባለቤትነት ይዞ ከመሥራት አንፃር ህብረተሰቡ ያበረከተው አስተዋፅኦ ይበል የሚያስብል ነው፤በቀጣይም ተጠናክሮ የሚቀጥል ተግባር ሊሆን ይገባል ብለዋል። አክለውም ከሰላም ስራችን ጎን ለጎን እየተሰሩ ያሉት የልማት ስራዎች የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ናቸው ብለዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *