Civil Service

በመንግስት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 309/2018 ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ፡፡

በሰሜን ሸዋ ዞን ሚዳ ወረሞ ወረዳ የሲቪል ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ጽ/ቤት በመንግስት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 309/2018 ዙሪያ ለፅ/ቤቱ ባለሙያዎች መስከረም 8/2019 ዓ/ም የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ።

የወረዳ ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ጽ/ቤት የሰዉ ሀብት አስተዳደር ቡድን መሪ ወ/ሮ መሰረት እሸቴ በዛሬው እለት ለፅ/ቤቱ ባለሙያዎች በአዋጅ ቁጥር 309/2018 ዙሪያ ስልጠና መሠጠቱ በአዋጅና መመሪያ መሠረት ተግባራትን ለመፈፀም የረዳናል በቀጣይ እንዲህ አይነቱ ስልጠና እንደሚቀጥል ገልፀዋል።

የስልጠናው ተሳታፊዎች አዋጁ በመንግስት ተቋማት ላይ ያለ ማንኛውንም ሰራተኛ መብትና ግዴታውን አውቆ ተወዳዳሪና የአገልጋይነት መንፈስ የተላበሰ ይሆን ዘንድ እንዴት እራስን ማዘጋጀት እንደሚያስፈልግ የሚጠቁም በመሆኑ በዚህ ልክ የግንዛቤ ስልጠና መሰጠቱ ተገቢ መሆኑን ተናግረዋል።

ወ/ሮ መሰረት አዋጁ የመንግሥት ሠራተኞች አስተዳደርና አደረጃጀት ፍትሐዊ፣ ቀልጣፋ፣ ውጤታማ እና ተደራሽ እንዲሆን በማድረግ የተገልጋዩን ማህበረሰብ ፍላጎትና ጥያቄ በአጥጋቢ ሁኔታ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል፣ የመንግሥትን የመፈፀም ብቃት በማጎልበት፣ የዜጎችን ፍላጎት የሚያረካ እና ወደ ተሻለ የዕድገት ደረጃ ሊያሸጋግር የሚያስችል በመሆኑ የግንዛቤ ስልጠናውን ሁሉም የመንግስት ሰራተኞች መውሰድ ይኖርባቸዋል ሲሉ አሳስበዋል።

See less