መስከረም 18/2019(ሚዳ ወረሞ ወረዳ ኮሚዩኒኬሽን)
በሰ/ሸዋ ዞን ሚዳ ወረሞ ወረዳ የአለም የቱሪዝም ቀን በአለም አቀፍ ለ47ኛ፣ በሃገራችን ለ39ኛ በወረዳችን ለ12ኛ ጊዜ “ድጅታል አጀንዳና ሠው ሠራሽ አስተውሎት ለቱሪዚም አድስ ቅኝት” በሚል መሪ ቃል ጥንታዊውና እና ታሪካዊ በሆነው በአቡነ መልከ ፄድቅ ገዳም ተከብሯል።
በፕሮግራሙ የሀገር መከላከያ ሠራዊት የ58ኛ ክፍለጦር ምክትል አዛዥ ኮለኔል ንጉስ ጣማለው፣ የወረዳዉ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሰይድ ኢብራሂም፣ የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሽፈራዉ ሃይሉ፣ ሌሎች የወረዳ አመራሮች፣የባህል ቱሪዚምና ስፓርት ጽ/ቤት ሃላፊና ሙያተኞች፣ የሀይማኖት አባቶችን ጨምሮ ከየሴክተሩ የተውጣጡ ባለሙያዎች ተገኝተዋል።
በፕሮግራሙ መክፈቻ ላይ የተከበሩ አቶ ሰይድ ኢብራሂም የቱሪዝም ቀንን ስናከብረ የአካባቢውን ታሪካዊ፣ ሃይማኖታዊና ተፈጥሯዊ የቱሪዝም ሀብቶች ለሀገር ውስጥና ለውጭ ጎብኚዎች በማስተዋወቅ፣ የቱሪስት ፍሰትን ለማሳደግ ነዉ፤
በመሆኑም ወረዳው የጀመራቸውን የዕድገት ጉዞ ለማስቀጠል ከቱሪስት መዳረሻ ማዕቀፍ ጋር በማስተሳሰር የተዳፈኑ ቅርሶችን በጥልቀት በማየት በማስተዋወቅ ለትውልድ የሚሻገር ድጅታላይዝድ ማድርግ እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል።
የገዳሙ አበሚኔት /አስተዳዳሪ/ የሆኑት ቆሞስ አባ ወልደማሪያም አባቡ በገዳሙ ውስጥ ያሉ ቅርሶችንና አጠቃላይ የገዳሙን ታሪካዊ አመሰራረት ለበዓሉ ታዳሚዎች አስጎብኝተዋል አስተዋውቀዋል።
የወረዳው ባህል ቱሪዝም እና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ላቀ ጋሻው በበኩላቸው የቱሪዝም ቀንን በጋራ ማክበር የአካባቢውን ባህላዊ እሴት ለማጠናከር፣ የቱሪዝም ሀብቶችን ለማስተዋወቅ እና ከቱሪዝም የሚገኘውን የልማት እድል ለማስፋት የሚያግዝ መሆኑ ገልፀዋል።
ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ የመጣው የቱሪዝም ቀን መከበር በዋናነት በወረዳችን የሚገኙ ቅርሶችን በማስተዋወቅ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ጎብኚዎች ቁጥር እንዲጨምር ያደርጋል ያሉተ የወረዳዉ ም/አስተዳዳሪና የሲ/ሰ/የሰዉ ሃብት ልማት ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አባይነዉ ወንድወሰን በወረዳችን ያሉ የቱሪዝም መዳረሻዎች ምንም እንኳ ሳቢና ማራኪ፣ እምቅ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ባለቤት ቢሆኑም በአግባቡ የገበያ ጥናትና የማስተዋወቅ ስራ በሰፊው ካልተሰራ አካባቢውን የቱሪስት መዳረሻ ማድረግ አይቻልም በመሆኑም ለሰላማችን ዘብ በመቆም ሁላችንም የበኩላችንን ድርሻ መወጣት ይጠበቅብናል ብለዋል።
በተጨማሪም አቶ ሰይድ ኢብራሂም ቱሪዝም ለአገር እድገት ከፍተኛ አስተዋጽዎ ያለው ሲሆን ለሰላማችን ቅድሚያ በመስጠት የወረዳውን የቱሪዝም ሀብቶች ለይቶ በማልማትና በማስተዋወቅ፣ የቱሪስት መዳረሻዎችን በማሳደግ፣ የቱሪዝም ዘርፉን ከአካባቢው ልማትና ኢኮኖሚ ጋር ማስተሳሰር ያስፈልጋል ብለዋል።
See less

