በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብሩ ላይ የወረዳ አመራሮችና ሰራተኞች፣ የሃይማኖት አባቶች፣በጎ ፈቃደኛ ወጣቶችና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዉበታል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የመራኛ 01 ቀበሌ አስተዳዳሪ አቶ ሞገስ አጎናፍር በበኩላቸው በዕለቱ ለከተማ ውበት የሚሆኑ፣ የተለያየ ዝርያ ያላቸው ችግኞች መተከላቸውን ገልፀው ለከተማዋ ገጽታ መዋብ የከተማዋ ነዋሪዎች፣ ወጣቶችና መንግስት ሰራተኞች በተቀናጀ መልኩ እየሰሩ መሆኑ ተስፋ ሰጭ የልማት ዕምርታ ነው ያሉት አቶ ሞገስ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቀጣይ የእንክብካቤና የክትትል ስራ በትኩረት በመስራት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
የወረዳዉ ግብርና ልማት ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ሻረዉ ከፈለኝ ይህ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር የተፈጥሮ ሚዛንንና አካባቢን ከመጠበቅ ባለፈ በየደረጃው ያለውን የህብረተሰብ ክፍል ለጋራ ልማት እና አንድነት የሚያነሳሳ መሆኑን ጠቁመው ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር እንዲሁም ከተሞች ለነዋሪዎቻቸው ምቹና ሳቢ እንዲሆኑ ፋይዳው የጎላ ነው ሲሉ አብራርተዋል ።
በመርሃግብሩ ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የወረዳዉ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ሸፈራዉ ሃይለ አረንጓዴ አሻራ ልማት የመደመር ትውልድ ዘመን ተሻጋሪ ታሪካዊ አሻራ ከመሆኑም በላይ በመንግሥት ከተነደፉ ኢንሼቲቮች አንዱና እጅግ ታሪካዊ ስኬት የተመዘገበበት ሲሆን ለመጭው ትውልድ ምንዳ የሚሆን ተስፋ የምናኖርበት የላቀ ተግባር ነው ብለዋል።
የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሰይድ ኢብራሂም ለተተኪው ትውልድ የተራቆተ መሬት ሳይሆን በአረንጓዴ የተሸፈነ መሬት ለማውረስ ሁሉም ዜጋ አገር በቀልና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞችን በነቂስ በመውጣት መትከልና በአግባቡ በመንከባከብ ንቁ ተሳትፎ ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።
በተጨማሪም አቶ ሰይድ ችግኝ መትከል አካባቢን ከማስዋብና የአየር ንብረት ለውጥን ከመቋቋም ባለፈ ለአገራዊ ልማት ትልቅ ሚና እንዳለው ገልፀዉ የተተከሉ ችግኞችን ሁሉም አመራርና ህዝብ በባለቤትነት የመጠበቅና የመንከባከብ ስራውን አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።
See less

