የሚዳ ወረሞ ወረዳ የሴት አመራሮች ፎረም የ2018 በጀት አመት እቅድ አፈፃፀም ገመገመ።

በሰ/ሸዋ ዞን ሚዳ ወረሞ ወረዳ የሴቶች ፎረም የ2018 በጀት ዓመት የስራ አፈፃፀም ግምገማና የ2019በጀት አመት ዕቅድ ትውውቅ መድረክ ተካሄደ።

በእለቱ የወረዳው ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊና የፎረሙ መሪ ወ/ሮ አየናቸው ጌታሁን፣ የወረዳው ሴቶች ህፃናት ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ሃላፊ ወ/ሮ ኤልሳ ማሞ እና የማህበራዊ ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ መድና መሃመድ፣አጠቃላይ የሴት አመራሮች እድሁም የመቶ አምስተኛ ክፍለ ጦር አደኛ ሻለቃ የሴት ወታደሮች ተገኝተዋል።

የወረዳው ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ እና የፎረሙ መሪ ወ/ሮ አየናቸው ጌታሁን ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ፎረሙ የሴቶች ተሳታፊነትና ተጠቃሚነትን ለማስቀጠልና የታዩ ክፍተቶችን ገምግሞ የተሻለ ለመፈፀም የሚያስችል መድረክ መኾኑን ገልፀው መጭው አመት የሰላም፣ የፍቅር፣ ያንድነት፣የመረዳዳትና የመደጋገፍ እዲሆን ተመኝተዋል።

በዕለቱ የተዘጋጀዉን የሪፖርት ፎረም ሰነድ የወረዳው የማህበራዊ ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ መድና መሃመድና ሴቶችና ህጻናት ጽ/ቤት እቅድ ዝግጅት ባለሙያ ወ/ሮ ሃይማኖት ማሞ በጥንካሬና በድክመት በዝርዝር አቅርበው ሰፊ ውይይት እና ግምገማ ተካሂዷል፡፡

የእለቱን የውይይት መድረክ የወረዳው ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊና የፎረሙ መሪ ወ/ሮ አየናቸው ጌታሁን፣ የወረዳው ሴቶች ህፃናት ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ሃላፊ ወ/ሮ ኤልሳ ማሞ እና የማህበራዊ ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ መድና መሃመድ መርተውታል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች በበጀት አመቱ በበጓ ፈቃድ የተሰራው ስራ ከመቸውም በላይ የላቀ ስራ ተሰርቷል ያሉ ሲሆን የተጀመረውን የበጎ ፈቃድ ስራ አጠናክሮ መቀጠል እደሚገባና የተቸገሩ፣ የተጎዱ ሴቶችን ድጋፍ ማጠናከር እና እህታማችነትን ማጽናት እንደሚገባ ገልፀዋል።

የማህበራዊ ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ መድና መሃመድ የተሰበሰበው ደብተር በፍትሃዊ እድከፍፈል የበኩላችንን እሰራን ነው ብለዋል።

የወረዳው ሴቶች ህፃናት ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ሃላፊ ወ/ሮ ኤልሳ ማሞ በክረምት የበጓ ፈቃድ ስራ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ላደረጉ መስሪያ ቤቶች፣ባለሃብቶችና ግለሰቦች ልባዊ ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን የበጋ በጎ ፈቃድ ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥላል፤ ለዚህም ቅን ልቦች ለወገን ያላቸውን አጋርነት የበለጠ ማጠናከር ይኖርባቸዋል ብለዋል።

የወረዳው ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊና የፎረሙ መሪ ወ/ሮ አየናቸው ጌታሁን የዛሬው ፎረም ለየት የሚያደርገው ጀግኖች የሴት መከላከያ ሰራዊት አባል እህቶቻችን በተገኙበት መሆኑን ገልፀው፤ በባጀት ዓመቱ የተሰበሰበውን የመማሪያ ቁሳቁስ ለወላጅ አልባ ህፃናት ተደራሽ እድሆን ሁላችንም የበኩላችንን መስራት ይኖርብናል ሲሉ ገልፀዋል።

በመጨረሻም በ2019 ዓ/ም የሚከናወኑ ተግባራት ላይ የቀጣይ አቅጣጫ የተቀመጠ ሲሆን ለሴት ወታደሮቹ ለእያንዳንዳቸው 3ሺ ብር እና የንፅህና መጠበቂያ ተበርክቶላቸው ፎረሙ ተጠናቋል።

See less

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *