በሚዳ ወረሞ ወረዳ የ2019 የትምህርት ዘመን የትምህርት መማር ማስተማር ሥራ በይፋ ተጀመረ።

በሰ/ሸዋ ዞን ሚዳ ወረሞ ወረዳ ሁሉም ትምህርት ቤቶች የ2019 የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ሂደት መስከረም 5 /2019 ዓ/ም ተጀምሯል።

የወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት እቅድ ዝግጅት ሃብት ማፈላለግ ቡድን መሪ አቶ ወድምኩን ክበበው በወረዳው ባሉ አጠቃላይ ትምህርት ቤቶች የአድሱ የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ስራ በይፋ መጀመሩን ገልጸዋል።

ለትምህርት ዘመኑ አስፈላጊ የሆኑ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ሲከናወኑ መቆየታቸውን ያነሱት አቶ ወድምኩን ለትምህርት የደረሱ ህጻናት፣ ያቋረጡና በነባር ሲማሩ የነበሩ ተማሪዎች በትምህርት ገበታቸው ላይ እንድገኙ እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ለመማር ማስተማር ስራው ውጤታማነት የወላጆችና የትምህርት ማህበረሰቡ ድርሻ የጎላ መሆኑን ጠቅሰው ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት እንድመጡ ሁሉም የበኩሉን ሚና እንድወጣ አሳስበዋል።

See less

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *